8

የኢሬቻ በዓል ምንም ዓይነት ጉዳትና ግጭት ሳያስተናግድ በሰላም ተጠናቋል

(ኢሬቻ፣ጥቅምት 1, 2017) የኢሬቻ በዓል ምንም ዓይነት ግጭት ሳይከሰት በሰላም መጠናቀቁን የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት አስታወቀ። በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዲ በየዓመቱ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ዛሬም በተለየ ድምቀት ተከብሯል።

የበዓሉ ታዳሚዎች የልምላሜ ምልክት የሆነውን እርጥብ ቄጤማና አበባ ይዘው ወደ ሐይቁ  በመውረድ ነው አምላካቸውን በማመስገን በዓሉን ያከበሩት።

በበዓሉ ላይ ስድስት ሚሊዮን ህዝብ ይታደማል ተብሎ ቢጠብቅም  የተገኘው ህዝብ  ከሰባት ሚሊዮን በላይ የሚገመት መሆኑ ልዩ ስሜት ፈጥሮባቸዋል፡፡

“ይህ ሁሉ ህዝብ በአንድ ላይ በዓሉን አክብሮ ምንም ዓይነት ግጭትና የአካል ጉዳት ሳይደርስ መለያየቱ ትልቅ ስኬት” መሆኑን ገልጸው  ኅብረተሰቡ ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የሰላም አስከባሪ ወጣቶች አስተባባሪ ወጣት ለማ ገመቹ በበኩሉ  ወጣቶች በዓሉ በሰላም እንዲካሄድ  የተሰጣቸውን ተልዕኮ በስኬት ማጠናቀቃቸውን ገልጿል።

የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር የተሰጣቸው ሃላፊነት ትልቅ መሆኑን የተናገረው ወጣቱ፤ “ለተሳታፊ ወጣቶች ቀጣይ ስራ ጥሩ ልምድ ይሆናቸዋል” ብሏል።

ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተገኙና በባህላዊ አልባሳት ያሸበረቁ አባ ገዳዎች፣ ወጣቶች፣ የተለያዩ የህብርተሰብ ክፍሎች ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ እሬፈና ወይም የምስጋና ስርዓት በማድረስ በሰላም ተመልሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *